ስላቫዊ ቋንቋዎች
Appearance
(ከስላቪክ ቋንቋዎች የተዛወረ)
![](http://chped.net/https/upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/e6/Slavic_languages_map_en.svg/330px-Slavic_languages_map_en.svg.png)
ስላቫዊ ቋንቋዎች ወይም ስላቪክ ቋንቋዎች አንድ የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ናቸው። ከባልታዊ ቋንቋዎች ጋራ አንድላይ የባልቶ-ስላቫዊ ቋንቋዎች ቅርንጫፍ ይሠራሉ።
ስላቫዊ ቋንቋዎች ሁሉ ከቅድመ-ስላቭኛ ደረሱ፤ እሱም ከቅድመ-ባልቶ-ስላቭኛ እንደ ደረሰ ይታስባል።
የስላቫዊ ቅርንጫፍ ሦስት ክፍሎች ምሥራቅ ስላቫዊ፣ ምዕራብ ስላቫዊ እና ደቡብ ስላቫዊ ናቸው።