Jump to content

ማቴዎስ መንገሻ

ከውክፔዲያ

ማቴዎስ መንገሻ1978 ሰኔ 23 እንደ ኢትዮጲያ አቆጣጠር በአዲስ አበባ ከተማ ከእናቱ ከወ/ሮ አዲስ በቀለ እና ከአባቱ መንገሻ መጃ ተወለደ ፡፡ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በሚገኘው ብርሃንና ሰላም ና የካቲት 23 አንደኛ ደረጃዎች ከተማረ በኃላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በከፍተኛ 7 2ኛ ደረጃ ተከታትሏል በመቀጠልም ከአድማስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ በዲግሪ ተመርቆ በግል ድርጅቶች ለአራት አመታት ተቀጥሮ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ የራሱን የግል የልብስ መሸጫ ቡቲክ እና የሞባይል መሸጫና የጥገና ማእከል በወላይታ ሶዶ ከተማ በመክፈት ህብረተሰቡን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በ2009 ዓ.ም ደግሞ ከወይዘሪት ሠላም አሰፋ ጋር ጋብቻ የፈፀመ ሲሆን ሔማን ማቲዎስ ተብላ የምትጠራ የአንዲት ሴት ልጅ አባት በመያዚያ 15, 2010 ዓ.ም ሆኗል፡፡