Jump to content

ቀንድ

ከውክፔዲያ
ረጃጅም ቀንዶች ያሉት የስኮትላንድ በሬ

ቀንድ በአንዳንድ አይነት እንሳሳ ራስ የሚገኝ ጫፍ ነው። ከኬራቲን የተሠራ ዕውነተኛ ቀንድ የሚገኝባቸው እንስሳት ላም በሬ ጎሽ ፍየል ሚዳቋ ዋልያ ወዘተ. (የቶራ አስተኔ) ናቸው። የአውራሪስ ቀንድና የፈረንጅ አጋዘን ቀንድ ሌሎች አይነቶች ናቸው። የፈረንጅ አጋዘን ቀንድ እንዲያውም ከኬራቲን ሳይሆን በየአመቱ የሚበቅል አጥንት ነው።

በጥንት አይሁዶችአውራ በግ ቀንድ 'ሾፋር' የሚባል ሙዚቃ መሣርያ ይሠሩ ነበር። በብዙ ዘመናት ላይ ደግሞ ቀንዶች ለመጠጫ እንዲሁም ባሩድ ለመሸከም ይጠቅሙ ነበር።