ተውላጠ ስም
Appearance
ተውላጠ ስም በሰዋስው ለሰው ወይም ነገር ስም ምትክ ሊሆን የሚችል ተራ ቃል ነው።
ምድብ ተውላጠ ስም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በአማርኛ ዋና ምድብ ተውላጣ ስሞች እንዲህ ናቸው፦
- 1ኛ ነ. ፡ እኔ
- 2ኛ ነ. ፡ አንተ / አንቺ / እርስዎ
- 3ኛ ነ. ፡ እርሱ / እርሷ / እርሳቸው
- 1ኛ ብ. ፡ እኛ
- 2ኛ ብ. ፡ እናንተ
- 3ኛ ብ. ፡ እነርሱ
እያንዳንዱ ቋንቋ ለየራሱ የተለየ ምድብ ተውላጠ ስም አከፋፈል ዘዴ አላቸው፤ እንደ ጾታ፣ ቁጥር ወይም ለተናጋሪዎች ግንኙነት ወይም ክብር ረገዶች የተመሠረተ አከፋፈል ሊሆን ይችላል።