Jump to content

አርባ ልጆች

ከውክፔዲያ

አርባ ልጆች የተባሉት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የቱርክ መንግስት አርመናውያን ላይ ጭፍጨፋ ባካሄደበት ወቅት ወላጆቻቸውን በማጣት እና ከጭፍጨፋው ለማምለጥ ተሰደው በእየሩሳሌምአርመን ገዳም ውስጥ ሲኖሩ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ (ያኔ አልጋወራሽ ራስ ተፈሪ) አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው ያሳደጉዋቸው 40 አርመናውያን ልጆች ናቸው። በልጆቹ የሙዚቃ ችሎታ የተደመሙት አፄ ኃይለሥላሴ በእየሩሳሌም የአርመን ፓትርያርክን ፍቃድ ካገኙ በኋላ ልጆቹን ወደ ኢትዮጵያ ወስደው ተጨማሪ የሙዚቃ ስልጠና እንዲያገኙ አድርገዋል። ልጆቹ በሴፕቴምበር 6፣ 1924 እ.ኤ.አ. ዓ.ም. ከሙዚቃ ባንዱ መሪ ከኬቮርክ ናልባንድያን ጋር ኢትዮጵያ የደረሱ ሲሆን እነዚሁ ልጆች ናቸው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሙዚቃ ጓድ (የንጉሱ የሙዚቃ ጓድ የተባለውን) ያቋቋሙት። ኬቮርክ ናልባንዲያን ማርሽ ተፈሪ የተሰኘውን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ሆኖ እስከ እ.ኤ.አ. 1930-1974 ያገለገለውን ሙዚቃ (ግጥሙ የዮፍታሄ ንጉሴ ነው) የደረሰ ነው።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]