Jump to content

የምዕራብ ንጉሥ እናት

ከውክፔዲያ
«የምዕራብ ንጉሥ እናት» የሸክላ ቅርስ፣ 200 ዓ.ም ግድም ተሠራ

«የምዕራብ ንጉሥ እናት» (ቻይንኛ፦ «ሺ ዋንግሙ») በቻይና አፈ ታሪክ ትገኛለች።

ቀርከሃ ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በንጉሥ ሹን ፱ኛው ዓመት (2052 ዓክልበ. ግድም) መልዕክተኞች ከምዕራብ ንጉሥ እናት (ሺ ዋንግሙ) ወደ ሹን ግቢ መጥተው «የነጭ ድንጋይ ቀለበቶችና የዕንቁ የቀስተኛ ጣት ቤዛዎች» ስጦታ አቀረቡ። በሌላ ምንጭ (ሹንዝዕ) የሹን ተከታይ ዳ ዩ የሺ ዋንግሙ ተማሪ ነበረ።

ከዚህ በኋላ በቻይና አረመኔ ሃይማኖት ሺ ዋንግሙ እንደ ሕያው ሴት አምላክ ተቆጠረች። በሥነ ቅርስ ከሻንግ ሥርወ መንግሥት (1700 ዓክልበ. ግድም) የተቀረጸ አጥንት በጸሎት ይጠቅሳታል። በ950 ዓክልበ. አካባቢ የነገሠው ዦው ሙ እንዳገኛት በትውፊት ይባላል። በ4ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ላውዝዕ ያስተማረው የዳው ሃይማኖት ደግሞ እስካሁን እንደ ሴት አምላክ ያያታል። በተጨማሪ የቻይና ነገሥታት ጪን ሽኋንግ (250 ዓክልበ. ግድም) እና ሃን ዉ (100 ዓክልበ. ግድም) እንዳገኙአት በትውፊት ይባላል።