Jump to content

የቻይና ታላቅ ግድግዳ

ከውክፔዲያ
የቻይና ታላቅ ግድግዳ በዘመናት ላይ

የቻይና ታላቅ ግድግዳቻይና ስሜን ጠረፎች ላይ ከጥንት ጀምሮ የተሠሩት የግድግዶች ጣቢያ ነው።

ከ800 ዓክልበ. ጀምሮ የቻይና መሪዎች የስሜኑን ነገዶች ለመከልከል ግድግዶች ያሠሩ ነበር። እንደ ሥዮንግ-ኑ የመሠሉት ስሜናዊ ብሔሮች በየጊዜው በሠረገላዎች ቻይናን የወረሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ ይህም ግድግዳ መሰናከል ኢንዲሆንባቸው ታሰበ።

በዘመናት ላይ ብዙ ሥርወ መንግሥታት ተጨማሪ ግድግዶች፣ የዘበኛ ግምቦችም፣ ተሠሩ ወይም ታደሱ ወይም ተሻሸሉ። በ4 ወይም 5 ሺህ ማይል ላይ ይዘረጋሉ። ይህም እስከ 1636 ዓም ማንቹዎች እስከ ተሻገሩት ድረስ ተቀጠለ።

የቻይና ታላቅ ግድግዳ