Jump to content

ጄነራል አስፋው ወልደ ጊዮርጊስ

ከውክፔዲያ

እኚኽ ስመ ጥሩ አርበኛ ጠላት ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለመውረር በመጣ ጊዜ፤ በቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ፤ በመሀል ደቡብ ክፍል የጦር ሠራዊት ደጃዝማች በየነ መርዕድ ዋና አዝማች፤ ረዳቶች በጅሮንድ ፍቅረ ሥላሴ ከተማ፤ ወንድማቸው ፊታውራሪ አጥናፍ ሰገድ ወልደጊዮርጊስ እና እሳቸው (ቀኛዝማች አስፋው ወልደጊዮርጊስ እንዲሁም 'ከጠላት ጋር ሆነን አገራችንን አንወጋም' ብለው ኢጣልያን ከድተው ከመጡት ኤርትራውያን ቀኛዝማች ሰላባና ቀኛዝማች አንዶም ጋር ዘመቱ።